የ2012 ት/ዘምን የተማሪዎች ጥሪ (2ኛና 3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ብቻ)
የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር መደበኛ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች መግቢያ ቀን መስከረም ቀን 25 እና 26/2012 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም ቀን 27 እና 28/2011 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነባር መደበኛ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ እንድተመዘገቡ ስንል እናሳውቃለን፡፡
በዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደፊት በሚድያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
= ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
= ተማሪዎች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (MoSHE) ይፋ የተደረገውን የኃላፊነት መውሰጃ ውል ሞልተው ከሚኖሩበት ወረዳ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም በማስመታት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
= በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (MoSHE) በተሰጠው መመሪያ መሰረት ውሉን ይዘው ያልመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው አያሰተናግድም፡፡
= የውል ቅጹን ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ www.kdu.edu.et እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ኦፊሻል ቴሌግራምና ፌስቡክ ፔጅ ( KEBRI DEHAR UNIVERSITY https://t.me/kduadmin ) / ( https://www.facebook.com/Kebri-Dehar-University-306587496533329 ) ላይ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት